የቀይ ባህር ምስጢር ፤ የኢትዮጵያ መብት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ የውሃ አካላት መካከል ልዩ እና ስልታዊ ስፍራ የሚይዝ ተፈጥሮ ነው። ባህሩ ከተለመደው የባህር ውቅያኖስ ባህሪ ይልቅ በርካታ ተፈጥሯዊ ምስጢራትን በውስጡ ይዟል። ቀይ ባህር በውሃው ንጹህነት እና በሰማያዊነቱ የሚታወቅ ቢሆንም “ቀይ” የሚለውን ስም ያገኘው ግን በየወቅቱ በውሃው ላይ በሚፈነዱ…
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ሶስት የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራረሙ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በ3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ተጨባጭ ትብብር የሚያሸጋግሩ ሶስት የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እና በሩሲያ ወገን መካከል የተፈረሙት እነዚህ ስምምነቶች፣ በጤና እና በሚዲያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ…
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞስኮ በተካሄደው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች↗
የኢትዮጵያና የሩሲያ ወዳጅነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በመከባበርና በአብሮነት አድጓል። እ.ኤ.አ. በ1896 የታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የሩሲያ ቀይ መስቀል ቡድን ቁስለኞቻችንን ለማከም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። ቡድኑም አንድ የሕክምና መመሪያ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተርጉሟል። ያ ትንሽ የሚመስል ነገር ግን ትልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነበር፤ ዕውቀትን ወደ ፈውስ ለውጧል።…
በአማራ ክልል የንግድ ማጭበርበሮችን የሚከላከል የኪው አር ኮድ ምስጢራዊ የደረሰኝ ሕትመት ተጀመረ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተሳሳተ ደረሰኝ የሚከናወኑ የንግድ ማጭበርበሮችን መከላከል የሚያስችል ባለ ኪው አር ኮድ ምስጢራዊ የደረሰኝ ሕትመት ተጀምሯል። የባለ ኪው አር ኮድ (QR Code) ምስጢራዊ የደረሰኝ ሕትመት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን ፈንታው በዚሁ…
አዲስ አበባ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ወደ አፍሪካ አህጉር ሲመጣ ለማስተናገድ ዝግጁ ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ወደፊት ወደ አፍሪካ አህጉር በሚመጣበት ጊዜ የአፍሪካ ሕብረት መዲና የሆነችው አዲስ አበባ መድረኩን ለማስተናገድ ዝግጁ ናት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ3ኛው ሩሲያ – አፍሪካ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ አዲሱ የሁለትዮሽና የአህጉራዊ ትብብር የድርጊት መርሃ-ግብር…
ታግዶ የቆየው የትግራይ ቴሌቪዥን በአዲስ ስያሜ ፍቃድ ተሰጠው↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ታግዶ የቆየውን የትግራይ ቴሌቪዥንን በአዲስ ስያሜ ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቀደም ሲል ታግዶ የነበረውን “የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ” የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ “የትግራይ ሚዲያ ኮርፖሬሽን” በሚል አዲስ ስያሜ በዛሬው ዕለት ማደሱን…
በምግብ፣ በኃይል እና በእውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረግን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በምግብ፣ በኃይል እና በእውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረገች ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በሞስኮ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በምግብ ረገድ ቀዳሚ ዓላማችን ሕዝባችንን መመገብ እና ለዘላቂ…
የሠራተኞችን የጡረታ ቁጠባ በጥብቅ ቁጥጥር የኢንቨስትመንት አስተዳደር ሥርዓት መጠበቅ ይገባል – እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሠራተኞችን የጡረታ ቁጠባ በጥብቅ ቁጥጥር፣ በግልጽነት እና በጥንቃቄ በተሞላ የኢንቨስትመንት አስተዳደር እና በጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት መጠበቅ ይገባል አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)። የአፍሪካ የመጀመሪያው “የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓቶችን ማቀናጀት ለአፍሪካ የመሠረተ ልማት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን”…
የኢትዮጵያና ሩሲያ ስትራቴጂካዊ ትብብር የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያና ሩሲያ ስትራቴጂካዊ ትብብር የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ…
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የምንጊዜም ምርጥ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2008 ያሳካው የባሎንዶር ሽልማት የምንጊዜም ምርጡ ተብሎ ተመርጧል፡፡ በፍራንስ ፉትቦል የተዘጋጀው የምንጊዜም ምርጡ ባሎንዶር የደጋፊዎች ምርጫ ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2008 ያሸነፈው ባሎንዶር በእግር ኳስ ተመልካቾች በተሰጠ ድምጽ…
ልዩ የአየር ላይ የማጥቃት ጥበብ የተላበሰው ሱ 35 4++↗
ፑጎቼቪስ ኮብራ የተሰኘውን የማጥቃት ልዩ አቅም አየር ላይ የሚያስመለክተው ሱ 35 4++ በዛሬው ዕለት የዓለምን ቀልብ የሳበ የበርካቶችን ትኩረት የሰረቀ መረጃ ከሞስኮ ሰማይ ስር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ 12 የሱ 35 የጦር ጄቶችን በይፋ ወደ አየር ኃይሏ ቀላቅላለች፡፡ በዓለም ላይ በወደር የለሽነቱ የሚነገርለት የሩሲያው ሱ 35 ምን…
የመከላከያ ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ከአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ጋር ተወያዩ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ከአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤምስበርገር ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ በወቅታዊ የደህንነት፣ የሰላም ግንባታ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ጦርነቱ በኢትዮጵያ ፍላጎት የተነሳ ባይሆንም፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግን የሕዝብ ደህንነትን ባከበረ መልኩ…
ታላቅ ሃገር ነን፣ ታሪካዊ ሃገር ነን፤ በዚያው ልክ አቅም መገንባትና ዝግጅት ያስፈልጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቅ ሃገር ነን፣ ታሪካዊ ሃገር ነን፤ በዚያው ልክ አቅም መገንባትና ዝግጅት ያስፈልጋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች ከሩሲያ በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በብዙ ጠላት የተከበበች ሀገር ናት፣…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች ርክክብን በተመለከተ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-↗
ከጥቂት ዓመታት በፊት አጠቃላይ የኢትዮጵያን ስጋት ለመቀነስ እንዲሁም በዓለም ሀገራት ዘንድ የአየር የበላይነትን ለመውስደ የሚደረገውን ሩጫ በመገንዘብ ከሩሲያ መንግሥት ጋር የሱ-35 4ኛ ትውልድ ኤር ክራፍት ስምምነት ፈጽመን ነበር፡፡ ስምምነቱ ጊዜው ደርሶ የመጀሪያው ዴሊቨሪ ስምምነት በ2027 ቢሆንም ከሬዚዳንት ፑቲን ጋር በህንድ በነበረን ቆይታ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያቀርቡልን…
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሻል ያለውን ቴክኖሎጂ መታጠቅ ችላለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሻል ያለውን ቴክኖሎጂ መታጠቅ ችላለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የሱ-35 የጦር ጄቶች ከሩሲያ በተረከበችበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት በብዙ መልኩ የኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል አቅሟን ትገነባለች ብለዋል። እንደ ከዚህ…
125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ መገጭ ግድብ ተጨመሩ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በተመረቀው የመገጭ ግድብ የቆሮሶ ዝርያ ያላቸው 125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ተጨምረዋል። የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ባለሙያ አቶ አበበ ፈንታሁን እንደገለጹት፤ ክልሉ ያለውን የዓሳ ሀብት ልማት ሰፊ አቅም ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ያለውን የውሃ አማራጭ…
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) “መደመር” መጽሐፍ ወደ ሩስኪ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “መደመር” መጽሐፍ ወደ ሩስያ ቋንቋ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ በሩሲያ የተዘጋጀውን የመጽሐፉ የምረቃ መርሃ ግብር ተገኝተው በመካፈላቸው ታላቅ ደስታና ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ይህ ታሪካዊ…
የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሷል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይሏ እያደረገችው ያለው ዝግጁነት ማንኛውንም ጥቃት ቀድሞ…
ኢትዮጵያና ሩሲያ በኢነርጂ ዘርፍ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢነርጂ ዘርፍ በተለይም የሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን በመዘርጋት ረገድ የጠበቀ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ለኢነርጂ ዘርፍ ሰፊ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን፤ ዘርፉ የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የቀጣናዊ የኃይል ትስስር ማጠናከሪያ ምሰሶ…
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሩብ ዓመቱ ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጠረ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል አለ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ። የቢሮ ኃላፊ አሰለፈች መብራቱ እንደገለጹት ፥ በሩብ ዓመቱ ለ11 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ዕቅዱን በእጅጉ በማብለጥ 25 ሺህ 374…
አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች – የሩሲያና አፍሪካ የጎለበተ አጋርነት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አህጉር ናት፤ ነገር ግን ለዘመናት ሀብቶቿን ሌሎች ቅኝ ገዢዎች ሲጠቀሙበት ተመልካች ሆና ቆይታለች፡፡ አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ከተላቀቁ በኋላ የራስን ችግር በራስ የመፍታት ፍላጎታቸውን ለማሳካት የጋራ ትብብራቸውንም ለማጠንከር እንደ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አፍሪካ ህብረት) ያሉ…
የኅብረ ብሔራዊነት ማሳያ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነትና አንድነት ከማስከበር ባለፈ፤ የኅብረ ብሔራዊነት ህያው ምስክር ነው። ይህ ሠራዊት ባለፉት ዘመናት አደረጃጀቱና ዘመናዊነቱ ቢቀያየርም፤ አንድ የማይለወጥ መሠረታዊ መለያ አለው፡፡ እሱም ከተለያዩ ብሔሮች ብሔረሰቦች የተወጣጡ ውድ ልጆችን በአንድ ዓላማ አስተሳስሮ የሀገርን ዳር…
ኢትዮ- ሩሲያ፦ ከትናንት እስከ ዛሬ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሩሲያ እና በአፍሪካ አህጉር መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት በጋራ ጥቅም፣ በእኩልነት እና ሉዓላዊነት መርሆች ላይ ተመስርቶ ወደ አዲስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው። ዛሬ እና ነገ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የበርካታ…
የመደመር እሳቤ በተግባር የተገለጠባት አዲስ አበባ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያብራራው፣ ልማት ማለት ከአካላዊ ግንባታ በላይ የሆነ፣ ሰውን ማዕከል ያደረገ፣ ሀብቶችን በተቀናጀ መንገድ የሚጠቀም፣ የሕዝብ ተሳትፎን የሚያጠናክርና የጋራ ብልጽግናን የሚያሳድግ ሂደት ነው። በዚህ እሳቤ መሠረት የከተማ ልማት መንገዶችን፣ ሕንፃዎችንና መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሩሲያ ገቡ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 3ኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ለመታደም ሞስኮ፣ ሩሲያ ገብተዋል። #PMOEthiopia The post ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሩሲያ ገቡ appeared first on Welcome to Fana Media Corporation S.C .
የኢትዮጵያና ሩሲያ ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ፣ የወታደራዊ፣ የባህል እና የፖለቲካ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተጀመረው በፈረንጆቹ 1898 ሲሆን፣ የመጀመሪያው የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በአዲስ አበባ ተቋቁሟል። ከዚያን ጊዜ እንስቶ እስካሁን የሀገራቱ…
ጠንካራ መከላከያ ሠራዊት – ለሀገራዊ ልማትና ለቀጣናዊ ዘላቂ ሰላም↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘመናዊ የጂኦፖለቲካ እና የጸጥታ ጥናቶች በጋራ ከሚስማሙባቸው ጉዳዮች አንዱ ልማትና ዘላቂ ሰላም ያለ አስተማማኝ የመከላከያ ኃይል ሊታሰብ እንደማይቻል ነው። የአንድ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥንካሬ ድንበር ከማስከበር ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገት ዋስትና የሚሰጥ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያበረታታ እና ለቀጣናዊ ትስስርም መሠረት…
የትግራይ ተስፋ – ከግጭት ወደ ሰላም፤ ከስቃይ ወደ ልማት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይን ህዝብ ለዓመታት ሲጨቁንና ሲረግጥ የቆየውን ህገወጡ የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊታችንና በሰላም ኃይሎች አከርካሬውን ተመትቶ ከተበተነ በኋላ፣ ሕዝቡ ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሸጋገረበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። የፌዴራል መንግሥት የክልሉ ህዝብ ከነበረበት ጭቆና እና አፈና እንዲወጣ እንዲሁም በግጭት ምክንያት…
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር በልማትም በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል – ኦርዲን በድሪ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር በልማትም በንቃት እየተሳተፈ ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ። የምስራቅ ዕዝ ከሀረሪ ክልል መንግሥትና ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ያስገነባውን ዘመናዊ የእጅ ኳስ ሜዳ በርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት…
በክልሉ ባለፉት 3 ወራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት ክልሉ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት በግብርና፣ በማዕድንና በሌሎች…