በትግራይ ክልል የትጥቅ ማስፈታትና ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ሂደት በድጋሚ ተጀመረ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትጥቅ ማስፈታት፣ ከታጠቁ ኃይሎች የመውጣት እና ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስን ያካተተው ሂደት እንደገና ተጀምሯል። በሂደቱ መቀጠል ከጦርነት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ የሚፈልጉ ታጣቂዎች የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በመቐሌ በሚገኘው የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የምዝገባ ማዕከል…
የተዘጉ አገልግሎቶች መመለሳቸው እና እንቅስቃሴ መጀመሩ ተስፋ ሰጥቶናል – የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተዘጉ አገልግሎቶች መመለሳቸው እና እንቅስቃሴ መጀመሩ ተስፋ ሰጥቶናል አሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች። በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የተለያዩ የአገልግሎት ተቋማት እንደገና መከፈታቸውና የንግድ እንቅስቃሴው መሻሻሉ ለትግራይ ሕዝብ የተስፋ ብርሃን እየፈነጠቀ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ አቶ እዮብ…
የዲሲፕሊን ልዕልና ባለቤት፦ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንድ ሀገር ህልውና፣ ሉዓላዊነት እና የህዝብ ደህንነትን ማስከበር ሂደት ውስጥ የጠንካራ የዲሲፕሊን ባለቤት የሆነ ሠራዊት ሚና ምትክ የለሽ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከረጅም ዘመናት የውጊያና ሀገር የማስከበር ታሪኩ ባሻገር፣ በልዩ ወታደራዊ ዲሲፕሊኑ እና ለህዝብ ባለው ታማኝነት የሚታወቅ የሀገር አለኝታ እና ጋሻ ነው።…
የፓን-አፍሪካኒዝም ቀለማት፤ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘመናት ታሪካዊ ለውጦች ውስጥ ሉዓላዊነቷን በማስጠበቅ የምትታወቀው ታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማዋ የህዝቦቿ የጋራ ማንነት መገለጫ ነው፡፡ በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት መሃል ላይ ጎልቶ በሚታይ ኮከብ የተወከለው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ የሀገሪቱን ልምላሜ፣ ተስፋ፣ ጀግንነት እንዲሁም ብዝሃነት ይገልጻል፡፡…
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ሕገወጡን ቡድን ጨርሶ ለማስወገድ እንታገላለን – የዓዲ ጉዶም ነዋሪዎች↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ሕገወጡን ቡድን ጨርሶ ለማስወገድ እንታገላለን አሉ የዓዲ ጉዶም ከተማ ነዋሪዎች። በትላንትናው ዕለት በትግራይ ክልል የአዲ ጉዶም ከተማ ነዋሪዎች በነጻነት ወደ አደባባይ በመውጣት፣ ሕገወጡ ቡድን በህዝቡ ላይ ያደርስ የነበረውን አፋኝ ስርዓት፣ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እና የልማት በደል በጽኑ…
ከኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ የሚባል ተሞክሮ አግኝተናል – የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ዘርፍ እያከናወነች ካለችው ተግባር በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ የሚባል ተሞክሮ አግኝተናል አሉ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሺቲማ። በምክትል ፕሬዚዳንቱ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ “በሥርዓተ ምግብ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት” በሚል መሪ ሐሳብ ለሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት…
ሚድሮክ በግሉ ዘርፍ ልዩ አሻራ ያሳረፈ ድርጅት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ልዩ አሻራ ያሳረፈና በሀገር ግንባታ ውስጥ የራሱን ድርሻ የተወጣ ተቋም ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሚድሮክ ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት÷ ሚድሮክ ሀገር በጠራችው ጊዜ ሁሉ…
የሀገር ክብርና የጀግንነት ድል የሚገለጸው ሰንደቅ ዓላማን ከፍ በማድረግ ነው – አቶ ሃይሉ አዱኛ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ክብርና የጀግንነት ድል የሚገለጸው ሰንደቅ ዓላማን ከፍ በማድረግ በመሆኑ፤ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነትና የሕዝቦች አንድነት ታላቅ መገለጫ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ፡፡ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያ…
የሠንደቅ ዓላማ ቀን ኢትዮጵያዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነትን በጋራ የምናጎለብትበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ። “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ መከበር የጀመረውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስጀምረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ በወቅቱ ባስተላለፉት…
ኢትዮጵያ፤ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ኢትዮጵያ በመሬት ስፋቷ ብቻ ሳትሆን በዘመናት የተሻገረ ታሪክ፣ በብዙ ትውልዶች የተገነባ ማንነት፣ በችግር ውስጥ ያልተሰበረ ጽናት እና ከዛሬ በላይ የሚመለከት ሕዝብ የተሸከመች ሀገር ናት። ትልቅነት ያለፈውን ማውራት ብቻ አይደለም፤ ትልቅነት ያለፈውን ወደ ነገ የመቀየር ብቃት ነው። የትናንትን ታሪክ የዛሬ ኃይል አድርጎ፣ የዛሬን…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሠንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት↗
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው። በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ…
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቀቀ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማውን አጠናቅቋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ በ90 ቀናት ዕቅድ መሰረት የክረምት በጎ ፈቃድ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የቤቶች ግንባታና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን…
በመደመር እሳቤ የቱሪስት መዳረሻነቷን ያጠናከረች ትልቅ ሀገር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የሚያስደንቅ መልክዓ ምድር የታደለችና በጥንታዊ ሥልጣኔ የገነነ ትልቅ ሕዝብ መገኛ ናት፡፡ ሀገሪቱ በባህል እና ቅርስ ሃብት የበለጸገች ብትሆንም፣ ይህንን ፀጋዋን በመጠቀም የሚገባትን ጥቅም ማግኘት ላይ ግን ችላ ብላ ቆይታለች። ዛሬ ግን የ’መደመር’ ፍልስፍና የጋራ አቅምና ችሎታዎችን በማቀናጀት አመርቂ ውጤቶችን…
ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአውሮፕላን በረራ እንደገና በመጀመሩ በጣም ተደስተናል – የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት እንደገና በመጀመሩ በጣም ተደስተናል አሉ የበረራ አገልግሎቱ ተጠቃሚ መንገደኞች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ወደ መቐለ ከተማ በረራ እንደሚጀምር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ዛሬ በይፋ ጀምሯል፡፡…
የኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማት ለቀጣናዊ ትስስር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ከማፋጠን ባለፈ ለቀጣናዊ ትስስርና ትብብር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው። የኢትዮጵያ የውሃ፣ ፀሐይ፣ ነፋስና ጂኦተርማል ብዝኅ የኃይል ፀጋዎች ልማት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅምን ማጎልበት የሚቻልበትን ምኅዳር እየፈጠረ ይገኛል፡፡ የታዳሽ ኃይል ልማት እመርታዊ ጉዞ…
ሊቨርፑል ከማንቼስተር ሲቲ፡ ተጠባቂው የአንፊልድ ፍልሚያ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ሊቨርፑልን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ምሽት 12፡30 ሰዓት በአንፊልድ በሚደረገው ጨዋታ ሊቨርፑል ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ለመመለስ ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ መሪነቱን ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡ ባለፉት 26 ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ወደ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል። የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቐለ ከተማ አርፏል። ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ ነው። የኢትዮጵያ…
የማያንቀላፋው ክንደ ብርቱ፡ የታጋሹ ጋሻ ወሰንና የላኪዎች ቀቢጸ-ተስፋ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰላምን ውድ ዋጋ ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ የስልጣኔና የታሪክ አርማ የሆነ የሀገር አለኝታ ነው። ይህ ግዙፍ ሠራዊት ውሳኔዎቹንና አቋሞቹን የሚቃኘው በታጠቀው ሃያል ወታደራዊ አቅምና የኃይል የበላይነት ልክ ሳይሆን፣ እንደ አንዲት ታላቅና ታሪካዊት ሀገር ጥልቅ አርቆ አሳቢነት ነው። ኢትዮጵያ ሰላምን…
በአእምሮና በአካል ብቁ የሆነ ትውልድ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአእምሮና በአካል ብቁ፤ በአስተሳሰብ ንቁ የሆነ ትውልድ በመደመር ተምሳሌት ከተማ እንገነባለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ዛሬ ማለዳ ከከተማችን ነዋሪዎችና አመራሮች ጋር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካሂደናል ብለዋል። በዚህ ወቅትም በአእምሮና በአካል ብቁ…
ከፉክክር ወደ ትብብር፡ ለብሔራዊ አንድነት↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና አካታች የፖለቲካ ምህዳርን መፍጠር የሚቻለው የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶቻቸውን በማክበር የሀገርን የጋራ ጥቅም በማስቀደምና በኃላፊነት ስሜት በጋራ መሥራት ሲችሉ ነው። በሀገር ግንባታ ሂደት የፖለቲካ ተቀናቃኝነት የግድ ወደ ጠላትነት መቀየር የለበትም። የተለያዩ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለሞችና አቋሞች…
ኢትዮጵያ በሉዓላዊነቷ አትደራደርም! ፤ ጠላትም በምሽጉ አይድንም↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታሪክ ምስክር ነው ፤ ኢትዮጵያ የተፈተነችበት ጊዜ ሁሉ የመከላከያ ሠራዊቷ የወርቅ መለያ ሆኖ አልፏል። ዛሬ በመደመር መንግሥት ሥር ነቀል ሪፎርም የጎለበተው የመከላከያ ሠራዊት ፣ ጀግንነቱን ከሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ከዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች ጋር አጣጥሞ ይዟል። የኢትዮጵያ ታሪክ ከውጭ ወረራና ከውስጣዊ ፈተናዎች ጋር…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለተለያዩ የፌደራል ተቋማት አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለተለያዩ የፌደራል የመደመር መንግሥት ተቋማት አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት 1. ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ 2. ጃፋር በድሩ — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ 3. ሃና…
ለዚህች ታላቅ ሀገር እና ታላቅ ሕዝብ የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ለመገንባት እየተሠራ ነው – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለዚህች ታላቅ ሀገርና ታላቅ ሕዝብ እንዲሁም ትልቅ ርዕይ ላለው መንግሥት የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው አሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል። ልዩ ኦፕሬሽን ስልጠና የወሰዱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በአፋር ክልል አዳይቱ ልዩ የኦፕሬሽን…
በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ ታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት የሚገኙባቸው አካባቢዎች↗
በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ መከላከያ ሠራዊት በማስረከብ ወደ ተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት እንዲገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት ለታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት የሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ በደቡባዊ ዞን ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችና አመራሮች – በማይጨው እና መኾኒ ከተሞች በደቡብ…
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ፡ ከዓባይ ውሃ እስከ ቀጣናዊ ትስስር↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለቀጣናዊ የጋራ ትብብር እና ልማት ቁልፍ ሚና የሚጫወት ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት አፍሪካውያን መቻላቸውን ያሳየና የጋራ ትብብር የት እንደሚያደርስ መመሰከሪያ ቁልፍ ንብረት ነው፡፡ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚከሰቱ እንደ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ እና ድርቅ ያሉ ከአየር ንብረት…
እናቅዳለን ፤ ብዙ ሳናስጮህ እንሰራለን ፤ ውጤት ለሕዝባችን እንናገራለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀው ስራ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ የፋብሪካው መገንባት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ወደ ውጭ ልካና ውድ ዋጋ ከፍላ መልሳ…
ወጥ የሆነ ሀገራዊ የህግ አተገባበርና አተረጓጎም እንዲኖር የሚያስችል ጉባኤ እየተካሄደ ነው↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጥ የሆነ ሀገራዊ የህግ አተገባበርና አተረጓጎም እንዲኖር የሚያስችል ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የማኅበረሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ በጉባኤው የተገኙ ውጤቶችን በማጽናት በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ጉድለቶችን ማረም አስፈላጊ…
አዲሱ የመደመር መንግሥት ለኢትዮጵያ መጻኢ እድገት↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታዋን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም የምታደርገው የሽግግር ምዕራፍ ነው። ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት ዓምስት ዓመታት እቅዶችዋ የሚሆናትን አዲስ የመንግሥት ምስረታ አካሂዳለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ…
የዛሬን ስኬት ወደ ዘላቂ ብሔራዊ ብቃት እየቀየርን የጋራ ሀገር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 ()ኤፍ ኤም ሲ) የዛሬን ስኬት ወደ ዘላቂ ብሔራዊ ብቃት እየቀየርን የጋራ ሀገር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር…
ለሕዝቡ የተገቡ ቃሎች በተግባር እንዲተረጎሙ የአፈጻጸምና የክትትል ሥርዓት ይጠናከራል – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሕዝቡ የተገቡ ቃሎች በተግባር እንዲተረጎሙ የታቀዱ ተግባራት በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የአፈጻጸምና የክትትል ሥርዓት ይጠናከራል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)። የክልሉ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት በ34ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ በጥልቀት እየገመገመ…