የመደመር መንግሥት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ መርሁ ነው – አቶ አረጋ ከበደ↗
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) – የመደመር መንግሥት የሚያከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃት መርሁ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ቤተ-መንግሥት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡ አቶ አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት ፥…
የዳንጎቴ ግሩፕ አክሲዮን ሽያጭ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መቅረቡ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት በር ይከፍታል – አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳንጎቴ ግሩፕ አክሲዮን ሽያጭ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በኩል መቅረቡ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት በር የሚከፍት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ። የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ከናይጄሪያው ግዙፍ ኩባንያ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር…
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት ዓለም አቀፍ ዕውቅና አገኘች↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት ባዘጋጀው “100 Women Heroes” ዓለም አቀፍ ዕውቅና አገኘች። የተባበሩት መንግሥታት የምግብና ግብርና ድርጅት በግብርና፣ በምግብ ሥርዓት እና በገጠር ልማት ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ዕውቅና ለመስጠት ያዘጋጀው “FAO 100 Women Heroes” ዓለም አቀፍ…
ዘመኑን ያልዋጀው የግብፅ “የእኔ ብቻ” ቅዠት↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ ዓባይ ወንዝ የተፈጥሮ ጸጋ በምስራቅ አፍሪካ እና በዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የዘለቄታ ሰላም፣ ልማት እና የጋራ እድገት ትልቁ ማስተሳሰሪያ ሊሆን ቢገባውም ግብፅ በዓባይ ተፋሰስና በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ስትከተለው የኖረችው መርህ-አልባ ፖሊሲ፣ ከታሪካዊ የወረራ ሙከራዎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊው የደህንነትና የዲፕሎማሲ…
አይ ኤም ኤፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል-ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር)፡፡ የአፍሪካ ብሔራዊ ባንክ ገዥዎች ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር በባንኮክ ተወያይተዋል፡፡ በመድረኩ ኢዮብ…
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም – የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የኤርትራ ሕዝብ ስጋት ሆኖ አያውቅም አለ የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል። የኤርትራ ሠማያዊ ማዕበል የዲፕሎማሲ ኃላፊ ዮኤል ዮሀንስ ፥ ለ35 ዓመታት ኤርትራን የግል እስር ቤት ያደረገው የኢሳያስ አፈወርቂ ሥርዓት የኢትዮጵያን የአብሮ መልማት ጥያቄ ጥላሸት ለመቀባት የሚሄድበት መንገድ የኤርትራ ሕዝብ አቋም…
የመደመር መንግሥት ዘላቂ የኢነርጂ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ ነው↗
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 5 ቀን 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ተደራሽ፣ አስተማማኝ፣ ተመጣጣኝ እና ዘላቂ የኢነርጂ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። ሁለተኛው የኢትዮጵያ ታዳሽ ኢነርጂ ጉባኤ “የኢትዮጵያን የታዳሽ ኢነርጂ ሽግግር በኢንቨስትመንት፣ በፈጠራና በትብብር ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል…
የውቅያኖስና የምድር መንታ፤ ከኢትዮጵያ እስከ ቀይ ባህር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀይ ባህር ለአፍሪካ ቀንድ በተለይም ለኢትዮጵያ ሰፊ የጨው ውሃ ሳይሆን ለዘመናት የታሪክ ትንፋሽ እና የንግድ መስመር ሆኖ የኖረ ሕያው ምስክር ነው። የቀይ ባህር እና የኢትዮጵያ ታሪክ የታሰረበት ገመድ ከተራ የወደብ ጥያቄ የተሻገረ እጅግ ጥልቅ የሆነ የታሪክ እና የስነ-ልቦና ትስስር አለው። የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ እና ዓለም…
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፍሬሕይወት ታምሩ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል አካታችነትን በማጎልበት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በትኩረት ይሰራል አሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ። ፍሬሕይወት ታምሩ ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል። ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአዲሱ የኢትዮጵያ ግራንድ ስትራቴጂ ለዘርፉ…
የህገ ወጡ ሕወሓት ቡድን ፍጻሜና የትግራይ ህዝብ የሰላም ተስፋ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ዘመኑን ሙሉ የሙጥኝ ያለው የሴራና ሰላም ጠል የፖለቲካ መስመር የትግራይን ህዝብ ለአስከፊ መከራና እልቂት በተደጋጋሚ ሲዳርገው ይስተዋላል። ይህ አካሄድ ድርጅቱ ካከተመለት ህልውናው ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት፣ የሰላም መንገዶችን ከመከተል ይልቅ ሀገር አፍራሽ እና ጠብ አጫሪ ድርጊቶችን ከመሰንዘር…
ከትናንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ የዲፕሎማሲ ቀን እየተከበረ ይገኛል። የዲፕሎማሲ ቀን መከበር ሀገራት ከጎረቤቶቻቸው እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት ጋር የፈጠሩትን ወዳጅነት እንዲሁም ያላቸውን ቁመና መለስ ብሎ ለማየት እድል ይከፍታል። ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለመመለስ የጋራ ደህንነትንም ለማስጠበቅ የጋራ ተጠቃሚነትና አብሮ የማደግ መርህን…
በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰራጨ ነው↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው። ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማዕከላዊ መጋዘን በመጀመሪያው ዙር የተጫነው ሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች በመከፋፈል ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በቢዱ ወረዳ ጊሪፎ ቀበሌ ለበርካታ ወገኖች ተደራሽ…
ከንቲባ አዳነች የመዲናዋን የለውጥ ተሞክሮ ለአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች አካፈሉ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናዋን የለውጥ ተሞክሮ ለአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችና ባለድርሻ አካላት አካፍለዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችንና ባለድርሻ አካላትን በአዲስ አበባ የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎችን አስጎብኝተናል ብለዋል። በዚህም የመዲናዋን የለውጥ…
የኢትዮጵያ ስኬትና የነገ ትውልድ ግንባታ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራት ለዘላቂ ህልውናቸው፣ ለኢኮኖሚ ዕድገታቸው የሚያደርጉት ጥረት የሚጀምረው ከትውልድ ግንባታ መሰረት ነው። ሀገርን በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ደግሞ ከሁሉ አስቀድሞ በህፃናት ቀዳማይ እድገት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ተተኪ የሌለው ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የነገን ብቁ፣ ጤናማና ኃላፊነት የሚሰማውን ዜጋ የመቅረጹ ሂደት…
ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ1ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ነገ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ያካሂዳል፡፡ ምክር ቤቱ በነገ መደበኛ ስብሰባው በህገ- መንግስቱ አንቀጽ 55/19/ እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 152 መሰረት የምክር ቤት ጉዳዮች…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተወያዩ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እጅግ ፍሬያማ የሆነ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።…
ከምግብ ባሻገር፤ የመኸር እርሻ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ያካሄደችው መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የምርት እድገት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ግብርናን ከባህላዊ የዕለት ጉርስ ፍለጋ አውጥቶ ወደ ዘመናዊ፣ ምርታማ እና ኢኮኖሚን ወደሚመራ የሃብት ምንጭነት ለመቀየር የተሄደበት ርቀት የኢትዮጵያን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ የልማት…
የባህር በር፤ የመበልጸግና የህልውና ጉዳይ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራትን ጥንካሬ እና የመበልጸግ አቅም ከሚወስኑ መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል የባህር በር ባለቤትነት በቀዳሚነት ይጠቀሳል። አብዛኛው የዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴና የሸቀጦች ዝውውር በውቅያኖሶችና በባህሮች ላይ የሚከናወን በመሆኑ፤ ቀጥተኛ መውጫ ማግኘት የትኛውንም ሀገር ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ከፍታ የመምራት ትልቅ አቅም አለው።…
መንግሥት የሰጠው ፈጣን ምላሽና የትግራይ ሕዝብ ድጋፍ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል በሕገወጡ ህወሓት ቡድን የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በፍጥነት የመመለስና በራስ አቅም የሰብዓዊ ድጋፍ በአስቸኳይ የማቅረብ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም የህገወጡን ቡድን ጸረ ሰላምና ጸረ ሕዝብ ድርጊት በማስቆም የሰላምና የልማት ዋልታነቱን በተግባር ባረጋገጠበት ቁርጠኛ ርምጃ የክልሉ…
የኢትዮጵያ አየር ኃይል፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገነባ የሉዓላዊነት ጋሻ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የአየር ኃይል ዘመናዊነት፣ የሰው ኃይል ብቃትና የሥራ ዝግጁነት ወሳኝ ሚና አላቸው። የሀገርን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የጦር መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች የመጠቀም አቅም፣ የሰው ኃይል ሙያዊ ብቃት፣ የውጊያ ዝግጁነትና በዲሲፒሊን የተመሠረተ የተግባር አፈጻጸምን…
ኢትዮጵያ እና ቻይና ትብብራቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ችን ሃይ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ለረጅም ዓመታት የቆየውን የሁለቱን ሀገራት ትብብር በተለያዩ መስኮች ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት አቶ አህመድ ሺዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ…
መቐለ ከተማ ወደ ቀደመው ሰላሟ ተመልሳለች – የከተማዋ ነዋሪዎች↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መቐለ ከተማ ሰላሟ ተመልሶ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች አሉ የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡ ከዚህ በፊት ህገወጡ ቡድን በመቐለና በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሲሰራ መቆየቱን ነዋሪዎቹ አንስተዋል፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በመቐለ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት÷ በቅርቡ ህገወጡ የህወሃት…
በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ተነስቷል አለ የከተማዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ። ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀና ለእይታ…
ፍትሕ ለዓባይ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)በዓለም አቀፍ መድረኮች የውሃ እጥረት አለብኝ የሚል ሰፊ የፖለቲካ ትርክት ለመገንባት የምትሞክረው ግብጽ በእውነቱ የውሃ እጥረት አለባት ወይስ የከፋ የውሃ አስተዳደር ችግርና ከፍተኛ የሃብት ብክነት? ሀገሪቷ በቅኝ ግዛት ዘመን በተፈረሙና ኢትዮጵያን ባገለሉ የ1929 እና የ1959 ውሎች መሠረት 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ…
ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረው የባሕር በር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ ከታሪክ፣ ከጂኦግራፊ እና ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የጋራ አጀንዳ ነው። የኢትዮጵያን ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ በዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ላይ ዋና አጀንዳ ማድረግ ተችሏል። ኢትዮጵያ የባሕር መዳረሻ ሳይኖራት የሕዝቦቿን ዘላቂ ልማትና…
የኢፌዴሪ የመደመር መንግሥት ተቋማት ውስጥ የተሾሙ አመራሮች ስም ዝርዝር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሰባት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት፦ 1. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ 2. ታምራት በየነ (ዶ/ር) – የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ 3. አቶ ብርሃኑ ፈይሳ – የመንግስት ረዳት ተጠሪ 4. ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ –…
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክ እና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት እና ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት ስማምነቱ ላይ የደረሱት በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን…
ልባችንን በኩራት የሚሞሉት መታያዎቻችን – ከምሰሶው ባሻገር↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከምሰሶው በብዙ ርቀት ከፍ ብሎ የሚታይ የኩራታችን ምንጭ፤ የኢትዮጵያውያን ህያው መታያ ቀለማችን ነው፡፡ የታላቅነታችን ምልክት የሆኑትን አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት የምናውቃቸው ገና በልጅነት በተኮላተፈ አንደበት ብሔራዊ መዝሙራችንን ስንዘምር ነው፡፡ ያኔ ሽቅብ አንጋጥጠን እያየን ከምሰሶው ጫፍ…
ተመልከት ሠንደቅህን፣ ተከተል አለቃህን↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ይህች ሰንደቅ ከጨርቅ በላይ ናት። ዓድዋ ላይ በደም የተነከረች፣ በወረራ ጨለማ ያልጠፋች፣ ከጋና እስከ ሴኔጋል በርካታ አፍሪካውያን የነጻነታቸውን ሠንደቅ ሲሰፉ ቀለሟን የቀዱላት ናት። ይቺን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ ጠላት ደጋግሞ ሊጥላት ሞከረ፤ ነገር ግን በአይበገሬ ጥቁር አናብስት ልጆቿ ጽናት ዛሬም ከፍ ብላ ከመውለብለብ…
የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ሥራ እየተካሄደ ነው – አቶ ሙስጠፌ መሀመድ↗
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን የማስፋፋት ሥራ እየተካሄደ ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ። ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በክልሉ ሶስተኛ የሆነውን ጅግጅጋ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡ በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት÷ መሶብ የአንድ ማዕከል…