አቶ አንተነህ ፈቃዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቶ አንተነህ ፈቃዱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟል። አቶ አንተነህ ፈቃዱ በጉባዔው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ በመፈጸም በይፋ ስራ ጀምረዋል። The post አቶ አንተነህ ፈቃዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ…
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር ) የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አድርጎ ሰየመ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አድርጎ ሾሟል። ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ በመፈጸም ስራ ጀምረዋል። The post የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር ) የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አድርጎ ሰየመ appeared…
የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሰየሙ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር መስራች ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በጉባዔው የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል፡፡ #ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ The post የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ…
ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ዘላቂ ምርታማነት↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት ዝቅትኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ጫናን ለመቀነስና የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡ እነዚህ ስትራቴጂያዊ ተግባራት በዋናነት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የከተሞች ማህበራዊ ሴፍቲኔት መርሐ ግብሮችና የገጠር የአየር ንብረት መቋቋም…
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት መከበር ጀምሯል፡፡ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓትን አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች በምርቃት አስጀምረዋል፡፡ በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ…
የመደመር መንግሥት ችግሮችን ወደ ዕድል እየቀየረ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ወደ ዕድል እየቀየረ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካው መስክ ታላላቅ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት÷ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ሆና ሳለች…
ለሉዓላዊነትና ለብሔራዊ ደህንነት መረጋገጥ የተወሰዱ ወሳኝ ርምጃዎች↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኤርትራ እና ግብፅ ዲፕሎማቶች ላይ ያሳለፈችው ውሳኔ የሀገርን ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተወሰደ ወሳኝ ርምጃ ነው፡፡ ኢትዮጵያ «ቅድሚያ ለጎረቤት» በሚለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መርህ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስር በማጠናከር ላይ ትገኛለች። በመከባበርና በሰጥቶ…
የአፋር ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የቀረቡለትን የተለያዩ ሹመቶች አፅድቋል። በዚህም መሠረት:- 1. ሐሚድ ዱላ- ምክትል ርዕሰ መሥተዳድርና እና መሬት ቢሮ ኃላፊ 2. ወልኦ አይትሌ – ዋና የመንግስት ተጠሪ 3. መሐመድ አህመድ ዓሊ -የርዕሰ መሥተዳድሩ የፖለቲካ ተወካይ 4. ኢብራሂም ዓሊ ዑስማን…
ኢሬቻ፡ የምስጋና፣ የይቅርታና ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምት ወቅት በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ፈጣሪ (ዋቃ) ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው። በዓሉ ለፈጣሪ ምስጋና ከማቅረብ ባለፈ፣ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ቁርኝት፣ የማኅበረሰብ እሴቶችንና የጋራ ሕይወትን የሚያሳይ ሥነ ሥርዓት ነው። በዚህ ሥርዓት ውስጥ ኢሬቻ ምስጋናን…
የካይሮ ቅዠት እና ተላላኪዋ አስመራ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ቀንድ የጂኦ ፖለቲካዊ መድረክ ላይ የሚታዩት ተለዋዋጭ ክስተቶች ፍንትው አድርገው የሚያሳዩት አንድ ሀቅ አለ፤ ይህም የካይሮ እና የአስመራ ስልታዊ ፍርሃት ምንጩ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የመሆኑ ነገር ነው። ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ፣ የሕዝብ ቁጥርና ስትራቴጂካዊ የበላይነት ተጠቅማ የቀጣናውን የኢኮኖሚ…
ሉዓላዊነትን የመጠበቅና የማጽናት ውሳኔ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት ወስናለች። ከዚህም በተጨማሪ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንዲወጡም ተወስኗል። ከዚህ ጋር በተያያዘም አንድ የግብጽ ዲፕሎማት በተመሳሳይ 48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። ውሳኔው የተላለፈው…
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ7ኛ ዙር የመጀመሪያ ታሪካዊ መስራች ጉባዔው ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የክልሉ አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል። በዚህም መሰረት፡- 1.ዶ/ር ደምሴ አድማሱ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር 2. ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ…
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:- እንኳን ለታላቁ የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢሬቻ የኦሮሞ ማኅበረሰብ የክረምቱን ዝናብና ፈተና አልፎ፣ ተፈጥሮ በአረንጓዴ ውበቷና…
የሐረሪ ክልል ም/ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የምስረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የምስረታ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ በጉባዔው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር፣ የክልሉን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ምክትል አፈ ጉባዔ እንዲሁም ሌሎች ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። በተስፋዬ ሃይሉ The post የሐረሪ ክልል ም/ቤት 7ኛ የሥራ…
አንድ የግብጽ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላለፈ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብጽ ዲፕሎማት የሆኑት አህመድ መሀረም አህመድ ሶሊማንን በኢትዮጵያ ተቀባይነት የሌለው ሰው በመሆኑ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር እንዲወጣ ተወስኗል አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የግብፅ አረብ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የዲፕሎማሲ ሰራተኛ የሆነው አህመድ መሀረም አህመድ ሶሊማንን…
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቋል፡፡ ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡- ◉ ከመገናኛ…
የክልሉ አዲስ አደረጃጀት ልማትን በአንድ ማዕከል ለመምራት ያለመ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል አዲስ አደረጃጀት አገልግሎቶችን በሁሉም ደረጃዎች ማቋቋም፣ ልማትን ከአንድ ማዕከል መምራት እና የልማት ስራዎችን ወደ ታችኛው መዋቅር ማውረድ ዋነኛ ዓላማው ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ። ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ባደረጉት ቆይታ…
የግብፅየዘመናት ሴራ እና የኢትዮጵያ የማይበገር የልማት ጉዞ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበራትን ብቸኛ ተፅዕኖና የበላይነት ለማስጠበቅ ስትል ኢትዮጵያን በውስጥ ግጭትና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ የመዝፈቅ ረጅም ታሪክ እንዳላት የውሃ ፖለቲካ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በስፋት የጻፉበት ጉዳይ ነው። ከ1950ዎቹ እስከ 1990ዎቹ ባሉት አራት አሥርተ ዓመታት ካይሮ…
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እውቅና ሰጡ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጥተዋል። በከተማ አስተዳደሩ በ2018 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና መርሐ ግብር ተከናውኗል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በከተማዋ…
ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት በአስመራ፣ ኤርትራ የሚገኘውን ኤምባሲውን…
የምስጋና፣ የይቅርታና የአብሮነት መገለጫ ፡ ኢሬቻ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዝናብ ወቅት አልፎ ምድር ወደ አረንጓዴነቷ ስትመለስ፣ ወንዞች የሚረጋጉበትና ከክረምት ወደ አዲስ ወቅት የሚሸጋገርበት ጊዜ ይመጣል። ከክረምት ወደ አዲስ ወቅት በሚደረገው በዚህ ሒደት የተፈጥሮ መታደስ ብቻ ሳይሆን የሰው ልብ ከቂምና በቀል ወደ ይቅርታ፣ ከመራራቅ ወደ መቀራረብና ከግጭት ወደ ሰላም ይሸጋገራል፡፡ ይህ ወቅት…
መንግሥት አካታች የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር የወሰደው ርምጃ የሚደነቅ ነው – የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር የወሰደው ርምጃ የሚደነቅ ነው አሉ በአዲስ አበባ ከተማ በምክር ቤት አባልትነት የተካተቱ እና በሥራ አስፈጻሚነት የተመረጡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባዔውን በትናንትናው…
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ፡ ኢትዮጵያ↗
ኢትዮጵያ ሰፊ ግዛት ብቻ ሳይሆን ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ፣ በብዙ ትውልዶች የተገነባ ማንነት፣ በችግር ውስጥ ያልተሰበረ ጽናትና ከዛሬ በላይ የሚመለከት ሕዝብ ያላት ሀገር ናት። ትልቅነት ያለፈውን ማውራት ብቻ አይደለም፤ ያለፈውን ወደ ነገ የመቀየር ብቃት ነው። ትልቅነት የትናንትን ታሪክ የዛሬ ኃይል አድርጎ የዛሬን እውቀት የነገ ስኬት አድርጎ መገንባት ነው። እዚህ ላይ የሕዝቡ…
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ የቀድሞ የምክር ቤት አባላት ሽኝት አደረጉ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ምክር ቤት አባላት የክብር ሽኝት አድርገዋል። ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፥ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተመርጠው ባለፉት 5 ዓመታት የመረጣቸውን ህዝብ ሲያገለግሉ ለነበሩ የከተማዋ ምክር ቤት አባላት የክብር አሸኛኘት አድርገናል…
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለኢትዮጵያ የሰጡት ክብርና ምስጋና↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ መንግሥትና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለው አሉ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደው የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ነው። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በመልዕክታቸው ፥ የፕሮጀክቱ…
ኢትዮጵያና ጃፓን የሩዝ ምርት ልማትን ማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ጃፓን የኢትዮጵያን የሩዝ ምርት ዘርፍ ማዘመን የሚያስችል የ375 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ተፈራርመዋል። አቶ አህመድ ሺዴ በዚህ ወቅት÷ የግብርና ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን፣ ለምግብ…
በአዲስ አበባና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፈቃድ አይሰጥም – የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ አይሰጥም አለ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ማሳሰቢያ፤ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እና…
የኢትዮጵያ ቀጣናዊ አብሪ ኮከብነት ሚና፡ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እያሳየች ያለው ፈጣን ዕድገት እና የቀጣናውን ሀገራት በጋራ የማልማት ጽኑ ቁርጠኝነት አፍሪካ በራሷ አቅም ተባብራ ማደግ የምትችልበትን አዲስ ምዕራፍ እየቀረጸ ይገኛል። በዚህ ረገድ ዛሬ እንዲሁም በዚህ ሳምንት የተከናወኑ ሁለት ታላላቅ ስትራቴጂካዊ የኃይል እና የኢኮኖሚ ትስስሮች የኢትዮጵያን ቀጣናዊ መሪነትነና አብሪ…
የጋምቤላ ክልል ም/ቤት የክልሉ መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሹመት አጸደቀ↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ የቀረበውን የክልሉ መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሹመት አፅድቋል። በዚህም መሰረት፦ 1.ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር)፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ 2. አቶ ኮንግ ኩላንግ ፡ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ 3. አቶ ቻም…
የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ለቀጣናው የኃይል ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)↗
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኬንያ መንግሥት በዛሬው ዕለት የተጀመረው የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ለቀጣናው የኃይል ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኬንያ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሐ ግብሩ…